ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages) ከ 2 ዓመት ከ 8 ወር እስከ 5 ዓመት ከ 10 ወር ለሆኑ ህጻናት የግምገማ (evaluation) ማዕከል ነው። በልጅ ትምህርት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የዕድገት መዘግየቶችን እና ዕክሎችን (disabilities) እንለያለን። ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages) የዲሲ የኅዝብ ትምህርት ቤቶች (DC Public Schools, DCPS) መርሃ-ግብር ነው። ሁሉም አገልግሎቶቻችን ነጻ ናቸው።
ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages) በቤታቸው የሚማሩ (homeschooled) የዲሲ ልጆችን ጨሞሮ በዲሲፒኤስ (DCPS) ትምህርት ቤት የማይከታተል ማንኛውንም የዲሲ ልጅ ሊገመግም ይችላል። እንዲሁም የዲሲ ነዋሪ ያልሆኑ ልጆች በዲሲ ውስጥ በግል ትምህርት ቤት ወይም የህጻናት እንክብካቤ ማዕከል የሚማሩ ከሆነ መገምገም እንችላለን። በህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች የተመዘገቡ ልጆችን መገምገም አንችልም።
ልጃችሁ - ከ2 ዓመት-ከ8 ወራት - በታች የሆኑ-ከሆነ፤ እባካችሁ፣ ‘ስትሮንግ ስታርት (Strong Start)’ን፣ የዲሲ የቅድመ ጣልቃ-ገብነት ፕሮግራም (DC’s Early Intervention Program)ን አነጋግሩ።
በቀደምትነት በምትጠቀሙበት ቋንቋችሁ፣ አገልግሎቶቻችንን የማግኘት መብት አላችሁ። ይህ፤ የማስተርጎም-አገልግሎት የሚሰጥ-ሰው እንዲቀርብ እና ወሳኝ-የሆኑ ሰነዶች እንዲተረጎሙላችሁ የመጠየቅ-መብትን ያካትታል። በቋንቋ እገዛ-ማግኛ ድንጋጌ (Language Access Act) ስር - ስለአላችሁ መብቶች፣ የበለጠ እወቁ።
(REFERRAL)ን ማድረግ
ወደ ‘ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages)’ ልጅን ለመምራት (refer ለማድረግ):
- በwww.earlystagesdc.org ላይ፣ የኦንላይን ቅጹን መሙላት (ለመምራት/refer ለማድረግ፣ ተመራጭ-የሆነው መንገድ-ነው)
- ተሞልቶ-የተጠናቀቀውን የመመራት ቅጽ (referral form)ን ወደ [email protected] ኢሜል ማድረግ
- በ(202) 698-8037 ደውሉ
- ወይም ተሞልቶ-የተጠናቀቀውን የመመራት ቅጽ (referral form)ን፣ ወደ (202) 654-6079 ፋክስ/ fax ማድረግ
በዕድገት ላይ ለሚደረግ የምልከታ-ምርመራ (developmental screening) ወይም ለግምገማ (evaluation)፤ ማንም-ሰው፣ ልጅን-መምራት (refer ማድረግ) ይችላል። ግምገማው ከመጀመሩ-በፊት፤ ‘ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages)’፣ ከወላጆች ስምምነት-መስጫ (consent) ማግኘት-ያስፈልገዋል። ልጁ እንዴት እንደሚጫወት፣ እንደሚማር፣ ወይም እንደሚያድግ -ማንኛውም ጥያቄዎች ካሏችሁ፤ መምራት (refer ማድረግ) በጣም-ጠቃሚ ነው።
የመመራት ቅጽ (referral form)ን፣ በአማርኛ ዳውንሎድ (Download) ማድረግ።
ያለኝ መብቶች ምንድናቸው?
እንደ - ከ‘መዘግየት (delay)’ ወይም ከ‘ጉዳተኝነት (disability)’ ጋር ለሚገኙ ወላጅ ወይም አሳዳጊ እንደመሆናችሁ፤ የተወሰኑ መብቶች አሏችሁ። ለተጨማሪ መረጃዎች፤ ሙሉ የክንውን-ሂደት የደህንነት-ጥበቃ (procedural safeguards)ን አንብቡ።
እኛን-አነጋግሩን
ዋከር-ጆንስ (Walker-Jones) (1125 New Jersey Ave, 3rd floor, NW Washington, DC 20001)
- (202) 698-8037
- በአጎራቦች-መኖሪያው ዙሪያ፣ ነፃ የ3-ሰዓት የመንገድ-ላይ መኪና-ማቆያ/street parking አለ።
- ወደ ‘ማውንት ቨርነን (Mt. Vernon)’/’ኮንቬንሽን ሴንተር ሜትሮባቡር (Convention Center Metrorail)’፤ (አረንጓዴ (green)/ቢጫ (yellow) መስመሮችን) እና፣ የ‘ዩኒየን ስቴሽን/Union Station’ ሜትሮ-ባቡር/Metrorail (ቀይ መስመር/red line) - በእግር-ለመሄድ በሚያስችል ርቀት ላይ ነው።
- 96፣ D4፣ እና P6 ሜትሮ-አውቶቡሶች/Metrobuses - በአቅራቢያው ይቆማሉ።
ሮን ብራውን (Ron Brown) (4800 Meade St, NE Washington, DC 20019)
- (202) 442-7201
- በአጎራቦች-መኖሪያው ዙሪያ፣ ነፃ የ2-ሰዓት የመንገድ-ላይ መኪና-ማቆያ/street parking አለ።
- ወደ ዲንውድ ሜትሮ-ባቡር/Deanwood Metrorail (ብርቱካንማ-ቀለም መስመር/orange line) - በእግር-ለመሄድ በሚያስችል ርቀት ላይ ነው።
- W4፣ U7፣ U4 ሜትሮ-አውቶቡሶች/Metrobuses - በአቅራቢያው ይቆማሉ።
አጠቃላይ የሆኑ-ጥያቄዎችን ለማቅረብ: [email protected]
ስለ ‘ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages)’ ለተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፤ የእኛን የመረጃ-ምንጭ መጽሐፍት-ቤት (resource library)፣ ጎብኙ።